ትልቁ የእግዚአብሔር እይታ፡- የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊ አመጣጥ መቃኘት በቮጋን ሮበርትስ (GOD’S BIG PICTURE: Tracing the Story-line of the Bible by Vaughan Roberts)

2000 ዓመታት ያህል ፈጅተው፣ በሁለት ቋንቋዎች እና በተለያዩ ኪነ-ድርሳን በአርባ ሰዎች የተጻፉ ስድሳ ስድስት መጻሕፍት፡፡ ስፍር ቁጥር በሌላቸው የተለያዩ መጠኖች እና ጥራዞች፣ ትርጉሞች እና ቋንቋዎች የታተመ ዓለም ዓቀፍ የላቀ ሽያጭ ያለው ምርጥ መጽሐፍ፡፡ በፍርድ ቤት መሐላ ይፈጸምበታል፣ በሃይማኖታዊ ሰዎች ትግል ተካሂዶበታል፣ በክርክሮች ወቅት ተጠቅሷል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ ተራ መጽሐፍ አይደለም፡፡ እንዴት አድርገን ነው መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መጀመር እና በሙላት መገንዘብ የምንችለው?

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ቮጋን ሮበርትስ ናቸው፡፡ በዚህ “ትልቁ የእግዚአብሔር እይታ” በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊ አመጣጥን እንድንቃኝ ያግዙናል፡፡

ቮጋን ሮበርትስ በአስደናቂ ቅኝታቸው፣ የመጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ክፍሎች የእግዚአብሔር መንግሥት በሚለው ዋና ጭብጥ ሥር እንዴት አንድ ላይ እንደሚገጣጠሙ በማሳየት፣ ትልቁን ሥዕል አቅርበውልናል፡፡ እርሳቸው መጽሐፍ ቅዱስን በመተማመን እና በመረዳት የምናነብበትን ማበረታቻቸውን እና ጠቃሚ መሣሪያዎቹንም ይሰጡናል፡፡ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዋና ርእሰ ጉዳይ፣ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንዲሁም በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ደኅንነት ይጠቁመናል፡፡

Leave a Reply

×