Selected:

ለማገልገል መጠራት:- መሥዋዕትነት የተላበሰ የአገልጋይነት መንፈስ በፓትሪክ ሙሪቲ ንያጋ- CALLED TO SERVE: The Spirit of Sacrificial Servant hood by Patrick Murithi Nyaga

ለማገልገል መጠራት:- መሥዋዕትነት የተላበሰ የአገልጋይነት መንፈስ በፓትሪክ ሙሪቲ ንያጋ- CALLED TO SERVE: The Spirit of Sacrificial Servant hood by Patrick Murithi Nyaga

SIM Books Ethiopia/Bible Based Book/

 

ለማገልገል መጠራት:-
መሥዋዕትነት የተላበሰ የአገልጋይነት መንፈስ

(Called to Serve:
The Spirit of Sacrificial Servanthood)

መሥዋዕትነት የተላበሰ የአገልጋይነት መንፈስ፣ ወደ ደቀ መዛሙርቱ የሚያስተጋባ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ አንድ አገልጋይ አገልግሎቱን እንዴት ለእግዚአብሔር ሊያቀርብ እና በዚያም ውስጥ ባሉት በረከቶች ሊደሰት እንደሚችል የሚያበስር ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ አገልጋዮችን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጥቂት ተግዳሮቶችን ይለያል ነገር ግን እነርሱን እንዴት እንደምናስወግድ አርቆ የሚያሳይን እውቀት በመስጠት፣ ተግዳሮቶቹን ከማወቅ በላይ ይሻገራል፡፡

ይህ መጽሐፍ የብሉይንና የአዲስ ኪዳንን የአገልጋይነት መርኆችን ታሳቢ በማድረግ፤ እንዴት በተጨባጭነት እንደሚሠሩ ያሳያል፡፡ ብዙ ሰዎች ከማገልገል ይልቅ መገልገልን ይወዳሉ፡፡ ይህንን መጽሐፍ በማንበባችሁ፤ በእርግጥም እናንተ አገልጋይ መሆን አለመሆናችሁን መናገር ትችላላችሁ፡፡

መጋቢ ፓትሪክ ሙሪቲ፣ በካዮሌ፣ ናይሮቢ ውስጥ የጎስፕል ሰለብሬሽን ሴንተር ዋና መጋቢ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስና በሥነ-መለኮት ትምህርት ከፓን አፍሪካ ክርስቲያን ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቋል፡፡ ከመጋቢነት ሚናው በተጨማሪም፣ በኬንያ ውስጥና በሌሎች አገሮች የጉባዔ ተናጋሪ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ከባለቤቱ ግሬስ ጋር ተጋብተው ጁዌል እና ሞስስ በሚባሉ ሁለት ልጆች ተባርከዋል፡፡

‹‹የሰው ልጅ ሊያገለግልና ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ መጣ እንጂ ሊገለገል አልመጣምና፡፡››
(ማርቆስ 10፥45፣ አ.መ.ት)

 

መግቢያ

የአገልጋይነትን ጥሪ በሕይወቴ ውስጥ ባኖረው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እያነሣሣኝ በነበረው በመንፈስ ቅዱስ ጉትጎታ ምክንያት ይህን መጽሐፍ ጻፍኩ፡፡ ከተጠራሁበት ጊዜ አንሥቶ የጌታችንን አምላክ በተለያዩ አቅጣጫዎች አገልግዬዋለሁ፡፡

የእግዚአብሔር መንግሥት አገልጋዮች ጥቂቶች መሆናቸውን በዓመታት መካከል አሳይቶኛል፡፡ ለተለያዩ ምክንያቶችና ዓላማዎች ቀን እና ሌሊት የሚሠሩ፣ ነገር ግን አገልጋዮች ያልሆኑ፣ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ብዙዎቹ የተቀጠሩ ሲሆኑ፣ ሌሎች እንዲያው በቀላሉ ሌላ ቦታ የለመለመ መስክን ለራሳቸው ለማመቻቸት የሥራ መቀጠሪያ መረጃ ታሪካቸውን በመገንባት ተልዕኮ ላይ ያሉ ናቸው፡፡

ታዲያ እውነተኛ አገልጋዮችን የምናገኘው ከወዴት ነው? የእውነተኛ አገልጋይነት መንፈስ እንዲገኝ ለሚደረገው ጩኸት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት አልችልም፡፡ ይህ መጽሐፍ የተወለደው ለእነዚህ ግፊቶች መልስ በመስጠት ውስጥ ነው፡፡ ክብሩ ለእግዚአብሔር ይሁን፡፡

የዚህን መጽሐፍ ገጾች ስታገላብጡ፣ ለአገልጋይነት ያላችሁን ጥሪ ታስተውሉ ዘንድ ጸሎቴ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፣ በሠራተኛና በአገልጋይ መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ አንድ ሰው ለአንድ ኩባንያ ስለ ሠራ ብቻ ወዲያውኑ እርሱ ወይም እርሷ አገልጋይ ነው/ናት ማለት አይደለም፡፡ መጽሐፉን ስታነብቡ፣ የእግዚአብሔርን ድምፅ ትሰሙ ዘንድ ጆሮዎቻችሁ እንዲከፈቱና ሕይወታችሁም ሥር-ነቀል ለውጥ ያገኘው ዘንድ፣ እናንተም እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ትሆኑ ዘንድ መልስ እንድትሰጡት ጸሎቴ ነው፡፡ ማገልገልን መማር በእጅጉ ትሑት የሚያደርግ እና ብድራት ያለው ተሞክሮ ነው፡፡

ይህ መጽሐፍ የተጻፈው ቀለል ካለ፣ የተግባራዊ አገልጋይ አተያይ አኳያ እንጂ፣ በነገረ-መለኮት ሊቅ አተያይ አኳያ አይደለም፡፡ እየጻፍኩ ያለሁት እባርካቸው ዘንድ እና አገልጋይነታቸውን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት በሁሉም ደረጃዎች ላይ ላሉ ሰዎች ነው፡፡

መሪዎች ወደ አገልጋይነት የሚወስደውን መንገድ ለእግዚአብሔር ሕዝቦች በሚያስተምሩበት ጊዜ ሊጠቀሙበት ወይም ሊያመሳክሩበት የሚችሉበት መገልገያ ነው፡፡ ይህንን መጽሐፍ በምታነቡበት ጊዜ፣ የልባችሁ ዐይኖች የሚከፈቱ፣ መንፈሳችሁም ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ መገለጥና ጥበብ የሚሳል ይሁን፡፡

ይህ መጽሐፍ የተጻፈው ቀለል ካለ፣ የተግባራዊ አገልጋይ አተያይ አኳያ እንጂ፣ በነገረ-መለኮት ሊቅ አተያይ አኳያ አይደለም፡፡ እየጻፍኩ ያለሁት እባርካቸው ዘንድ እና አገልጋይነታቸውን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት በሁሉም ደረጃዎች ላይ ላሉ ሰዎች ነው፡፡

መሪዎች ወደ አገልጋይነት የሚወስደውን መንገድ ለእግዚአብሔር ሕዝቦች በሚያስተምሩበት ጊዜ ሊጠቀሙበት ወይም ሊያመሳክሩበት የሚችሉበት መገልገያ ነው፡፡ ይህንን መጽሐፍ በምታነቡበት ጊዜ፣ የልባችሁ ዐይኖች የሚከፈቱ፣ መንፈሳችሁም ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ መገለጥና ጥበብ የሚሳል ይሁን፡፡

(ከመጽሐፉ ከገጽ 11 እና 12 የተወሰደ)

 

 

 

Description

“ሐሳቦችን ለማስተላለፍ መጻሕፍት መጻፍ የሚችሉ ብዙ ሰዎች አሉ፣ የጻፉትን ነገር መኖር የሚችሉት ግን ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ለማገልገል መጠራት በሚለው መጽሐፍ ውስጥ፣ መጋቢ ፓትሪክ ለአገልግሎት ያለውን ልብ ብቻ ሳይሆን በተግባር የተለማመዳቸውን ጭምር አካፍሎናል፡፡ ክርስቶስ ያስተማረን እና – ለስኬታማ አመራር ብቸኛው እንዲሁም ተፈትኖ የተረጋገጠው መርኅ፣ ማለትም አገልጋይነትን፣ ለመከተል ለሚፈልጉ ሁሉ ይህን መጽሐፍ  እጠቁማለሁ፡፡”

ባሪኔ ኤ. ኪሪሚ፣

ጸሐፊ እና አሳታሚ፣

ናይሮቢ፣ ኬንያ፡፡

 

WWW.simbooksethiopia.com

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “ለማገልገል መጠራት:- መሥዋዕትነት የተላበሰ የአገልጋይነት መንፈስ በፓትሪክ ሙሪቲ ንያጋ- CALLED TO SERVE: The Spirit of Sacrificial Servant hood by Patrick Murithi Nyaga”

Your email address will not be published.

×