ስለ ንባብ የሚነገሩ አባባሎች
SIM Books Ethiopia/Bible Based Book/

ስለ ንባብ የሚነገሩ አባባሎች

 • የማያነብ እንደ እንስሳ ነው፡፡
 • ማንበብ የነፍስ ምግብ ነው፣ መጻፍ ግን የነፍስ ትግል ነው፡፡
 • ንባብ የብርሃንና የጨለማ፣ የሞትና የሕይወት ያህል ነው፡፡
 • ምግብ እያለ የማይበላ፣ መጽሐፍ እያለ የማያነብ (ምን ይባላል?)
 • አለ ማንበብ ወንጀል ነው፡፡
 • ሳያነብቡ መኖር ጨለማ ውስጥ እንደ መኖር ነው፡፡
 • ንባብ ዓለምን ሕያው አድርጐ የሚያቆይ የሕይወት ምግብ ነው፡፡ (ከወረዳ የኰሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተገኘ)
 • ማንበብ እውቀት ለመቅሰምና ለማሠራጨት ይጠቅማል
 • የሚያነብ ጦሙን አያድርም፡፡ (ከታክሲ ላይ)
 • ማንበብ ያባንናል፣ ከእንቅልፍም ይቀሰቅሳል፡፡
 • አገልጋይ የማያነብ ከሆነ፣ ማር-የለሽ ቀፎ ነው፡፡
 • ያልተላገ እንጨትና የማያነብ ሰው አንድ ናቸው፡፡
 • ኰረኰንች መንገድና የማያነብ ሰው አንድ ናቸው፡፡
 • መጽሐፍ እውነተኛ ጓደኛ ነው፡፡
 • አንባቢዎች መሪዎች ናቸው – Readers are Leaders.
 • የሚያነብ ሰው የተባረከ ነው፡፡ (መጽሐፍ ቅዱስ)
 • ቅዱሳት መጻሕፍትን አለማንበብ የእግዚአብሔርን ኃይል አለማወቅ ነው፡፡
 • ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
 • መጽሐፍ ገዝተው በስጦታ ካበረከቱ፣ የማይጠፋ ሀብት አወረሱ፡፡
 • There is no friend like a book – እንደ መጽሐፍ ያለ ጓደኛ የለም፡፡

 

ምንጭ፡- ምሕረቱ ጴ. ጉታ፣ “የንባብ ባሕል እና ቤተ ክርስቲያን:- በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የንባብ ባሕል ዙሪያ የተደረገ አጠቃላይ ቅኝት”፣ 1999 ዓ.ም.፣ በኤስ አይ ኤም ሥነ ጽሑፍ ከታተመው መጽሐፍ እና ሌሎች የተለያዩ ምንጮች፡፡ ያጠናቀሩት የኤስ ኣይ ኤም ሥነ ጽሑፍ ክፍል ባልደረባ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጽጌ ናቸው፡፡

 

http://simbooksethiopia.com/wp-admin/post-new.php

 

Leave a Reply

×